ሂጃብዋን ጠምጥማ ለእምነትዋ ሟች እሷ
ቢቻል ትሰጣለች ቀንሳ ከነብሷ
የባሌዋ ቆንጆ ልቤን ወስዳው ማዶ
ባህሌ ከባህልዋ ተዋህዶ

እኔ ነኝ ከሸዋ እስዋ ነች ከባሌ
ዋናው መዋደዱ ነው አለቺኝ ውዴ
አኒ ከን ሸዋ ኢሼን ከን ባሌ
ዋናሳ አናፍ አቲ ወልጃለቹ ጄቴ ጃላሌንኮ

ደግነትሽ ሌላ የምትዎደጂ
መሰሰት አታውቂም ወተቱን ስትቀጂ
ልቤ ላይ ቆልፈሽ በይቁልፉን ጣይው
መቼም እንዳይገኝ እንድሞት ሳትከፍቺው
ውስጥሽ አቆዪው

ሂጃብዋን ጠምጥማ ለእምነትዋ ሟች እሷ
ቢቻል ትሰጣለች ቀንሳ ከነብሷ
የባሌዋ ቆንጆ ልቤን ወስዳው ማዶ
ባህሌ ከባህልዋ ተዋህዶ

እኔ ነኝ ከሸዋ እሷ ነች ከባሌ
ዋናው መዋደዱ ነው አለቺኝ ውዴ
አኒ ከንሸዋ ኢሼን ከን ባሌ
ዋናሳ አናፍ አቲ ወልጃለቹ ጄቴ ጃለሌንኮ

አቤት ስናስቀና እኛ ስንዋደድ
ይመስላል ድጋሚ እንደ አዲስ መወለድ
ቀለበት ሲጠልቅም ህይወት ሲታደስ
ማለት አይደለም ወይ ሁሌ መደገስ
ሁሌ እያለ ደስ

ሂጃብዋን ጠምጥማ ለእምነትዋ ሟች እሷ
ቢቻል ትሰጣለች ቀንሳ ከነብሷ
የባሌዋ ቆንጆ ልቤን ወስዳው ማዶ
ባህሌ ከባህልዋ ተዋህዶ

እኔ ነኝ ከሸዋ እሷ ነች ከባሌ
ዋናው መዋደዱ ነው አለቺኝ ውዴ
አኒ ከንሸዋ ኢሼን ከን ባሌ
ዋናሳ አናፍ አቲ ወልጃለቹ ጄቴ ጃለሌንኮ

እኔ ነኝ ከሸዋ እሷ ነች ከባሌ
ዋናው መዋደዱ ነው አለቺኝ ውዴ
አኒ ከንሸዋ ኢሼን ከን ባሌ
ዋናሳ አናፍ አቲ ወልጃለቹ ጄቴ ጃለሌንኮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *