[ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በአይኔ]2X


እንዲያው አንዳንዴ ይገርማል
ኧረ እንደው አንዳንዴስ ይደንቃል
እንዴት ተንዶ ፍቅራችን
ማነው ያራራቀን የእውነት ቃል
በጊዜ አስታከን በዘመን
እራስ መውደድን አስቀድመን
ይቅርታ ራቀ ካፋችን
ስናይ እየተቀማ ልባችን


#አንቃን ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
#አንቃን ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ
#አንቃን ከቁጣ አብርደህ ቅን ወዳጅ አርገህ አንቃን
#አንቃን የት ይደረሳል ምን ይወረሳል ይብቃን


አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ
ማረን እግዚኦ ማረን ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን ከክፋ አድነን


አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚ ፈተና
አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማርና


[ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በአይኔ]2X


በሀሜት በወሬ ታጅበን
በግላዊ ምቾት ተከበን
በዚች ጊዜአዊ ከንቱ ዓለም
ዘላለም ቋሚ ግን አንድ የለም
ንብረት ከሰው ልጅ አብልጠን
ክፋት ምቀኝነትን መርጠን
ዘመን አለፈ ስንኖር
የፅድቁን መንገድ የሚያሳይ አጥተን


#አንቃን ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
#አንቃን ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ
#አንቃን ከቁጣ አብርደህ ቅን ወዳጅ አርገህ አንቃን
#አንቃን የት ይደረሳል ምን ይወረሳል ይብቃን


አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ
እግዚኦ ማረን ማረን ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን ከክፋ አድነን


አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚ ፈተና
አፋ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማርና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *