ከፍ ከፍ ብዬ ከማጣ ፍቅር
ዝቅ ዝቅ ብል አልሰኝም ቅር
ሰው ወዶኝ ትልቅነቴም ይቅር
በሀገር ተፎክሬ ሁሉም ሰው ቢለኝ አንቱ
#ያለ_ፍቅር_ከንቱ
አይደላኝ ኧረ እኔ ስሜ በመፍራቱ
መውደድ ነው ኩራቱ

ከፍ ከፍ ብዬ ከማጣ ፍቅር
ዝቅ ዝቅ ብል አልሰኝም ቅር
ሰው ወዶኝ ትልቅነቴም ይቅር
ሳይጎላብኝ ስሜ ባልባል ጀግና ጌታ
ልኑር የትም ቦታ
አያርገኝ ኧረ እኔ ታላቁን እስክንድር
ባሻኝ እንዳድር

የዓለም የፍቅር ቀን ሲወሳ
ያቃል ባየው አበሳ
ለሱ ነው ልቤ የሚሳሳ
የሮማን ግንብ ያፈረሰው
ቢራራ ላፈቀረው ሰው

አጃቢው ቢሆንም ሚሊዮን
ሳይተካኝ በናፓሊዮን
አደራ ይስጠኝ ለ ጲዮን
አዛኞ እንደምትረዳኝ
ከሰው ጋር ታኑረኝ አዋዳ

አይፍራ
ወዶ የሚፀና
አይፍራ
ጠብቆ ቃልኪዳን
አይፍራ
ለሰው የሚኖር ሰው
አይፍራ
ቅርብ ነው ለመዳን

[አፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ
አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ
ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት
የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት]2X


ከፍ ከፍ ብዬ ከማጣ ፍቅር
ዝቅ ዝቅ ብል አልሰኝም ቅር
ሰው ወዶኝ ትልቅነቴም ይቅር
በሀገር ተፎክሬ ሁሉም ሰው ቢለኝ አንቱ
#ያለ_ፍቅር_ከንቱ
አይደላኝ ኧረ እኔ ስሜ በመፍራቱ
መውደድ ነው ኩራቱ

እርቄ ከፍቅር ጎዳና
አስቤ በገናገና
ተብዬ ለመኖር ጀግና
በፍርሃት ሰውን ለማራቅ
አይደንድን ልቤ እንደ ጎልያድ

እንደ ቂል ሲያሳየኝ ዘመንን
ታሪኳ ሲያመጣት በዓይኔ
ፍቅር ነች እራሷ ለኔ
ወጣቷ ያገሬ ንግስት
ሰው ነበር የልቧ ስስት

ተው ጌታ … አፍስብኝ ለዛ
ተው ጌታ … ከሰው እንዳልርቅ
ተው ጌታ … አርገኝ እንደ ዳዊት
ተው ጌታ … ቃሉ እንደሚያምርለት

አፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ
አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ
ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት
የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት

[አጉል ክብር አግኝቼ ፍቅር ከማጣ
ይበጀኛል እኔስ ከቤት ባልወጣ
ወትሮም ትልቅነት መምጫው መንገዱ
ሲሰጥ ነው ከላይ የሰው መውደዱ]2X

አፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ
አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ
ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት
የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *