ውስጤን ለማዳመጥ በዝምታ
እስኪ ልሂድ ደሞ ጭር ካለው ቦታ
ለልቤ ጓደኛ እራሴው ነኝ
ዛሬ ልስጠው ግዜ ላጫውተው ያጫውተኝ

ድንገት እንደነቃ እንደባነነ
ግራ መጋባቴ የሚል ወገን
አንዳንዴም ከራሴ ሳወራ ነው
ከውስጤ ሰላም ጋር የሚያኖረኝ

ከሰው ጋር እየኖርኩ ሰው ከረሳኝ
ውስጤም በዝምታ ሰሚ ካጣ
ታዲያ ለምን ብዬ አወራለው
እራሴን በጫወታ እስክቀጣ

ሰው ባጣ እስኪ ልየው ይከፋኝ እንደው
ኧረ አንዳንዴም በዝምታ አለ ጨዋታ

እንደቀላል እንጂ እንደ ብርቅ እንደ ብርቅ
አትቁጠረው ልቤ ተሰፍሮ ላያልቅ
ከዚ ሀገር ጩኸት ከዛ ሀገረ ሁካታ
አረፍ እንበል ልቤ ጭር ካለው ቦታ

ልቤ
እስኪ ረጋ ልቤ
አረፍ እንበል ልቤ


ውስጤን ለማዳመጥ በዝምታ
እስኪ ልሂድ ደሞ ጭር ካለው ቦታ
ለልቤ ጓደኛ እራሴው ነኝ
ዛሬ ልስጠው ግዜ ላጫውተው ያጫውተኝ

የዝምታ ቋንቋ ሰም ወርቁን
የዝምታ ጥልቀት ሚስጥር ቃል
ከራሱ የሚያወጋ ሰው ያውቀዋል
ነፍሱን ያዳመጠ ልክ እንደኔ

ታዲያ እኔ መች ሆነ ሰው ጠልቼ
ጭር ያለውን ስፍራ ያስወደደኝ
የመግባባት እርሃብ ጥም እንጂ
የዝምታን መንገድ ያስመረጠኝ

ሰው ባጣ እስኪ ልየው ይከፋኝ እንደው
ኧረ አንዳንዴም በዝምታ አለ ጨዋታ

እንደቀላል እንጂ እንደ ብርቅ እንደ ብርቅ
አትቁጠረው ልቤ ተሰፍሮ ላያልቅ
ከዚ ሀገር ጩኸት ከዛ ሀገረ ሁካታ
አረፍ እንበል ልቤ ጭር ካለው ቦታ

ልቤ
እስኪ ረጋ ልቤ
አረፍ እንበል ልቤ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *