ዓይኔማ አሀሀ አይፈልገው
ካንቺ አልፎ ማየትን
አካሌም አይታክተው
አብሮሽ መቆየትን

ውዴ ውዴ የኔው ነሽ
ስሜቴ በዓይን የሚገባሽ
ውዴ ውዴ የኔው ነሽ
ጨዋታ በዓይን የሚገባሽ

ወሰን አልባው ፍቅርሽ
ጠብቆኝ በስስት
አድርጎኛልና መንገዴን እንዳልስት
ላንኳኳለት ሁሉ ልቤ አይከፈትም
እንኳንስ አካሌ ሃሳቤ አይሸፍትም
የልቤ ንግሥት አድርጌሻለሁ
ውዴ እልሻለሁ

ውዴ ውዴ
ካንቺ ርቆ አይችልም ሆዴ
ውዴ ውዴ
የማልጠግብሽ ሆነሻል እንዴ
ውዴ ውዴ
ባንቺ ፍቅር ሰክኗል መውደዴ
ውዴ ውዴ
እስትንፋሴ ሆነሻል አንዴ

ዓይኔማ አሀሀ አይፈልገው
ካንቺ አልፎ ማየትን
አካሌም አይታክተው
አብሮሽ መቆየትን

ውዴ ውዴ የኔው ነሽ
ስሜቴ በዓይን የሚገባሽ
ውዴ ውዴ የኔው ነሽ
ጨዋታ በዓይን የሚገባሽ

ተፈጥሮ ነውና ይነጋል ይመሻል
ዓይኔ ግን በስስት ጨፍኖም ያይሻል
ከፀጉርሽ ቅንጣት አንዲቷም ዘለላ
ስትወድቅ አያሳየኝ ይከፋኛልና
ከጎኔ ቁሚ እስከ እድሜዬ አመሻሽ
ክፉ ሳይነካሽ

ውዴ ውዴ
ካንቺ ርቆ አይችልም ሆዴ
ውዴ ውዴ
የማልጠግብሽ ሆነሻል እንዴ
ውዴ ውዴ
ባንቺ ፍቅር ሰክኗል መውደዴ
ውዴ ውዴ
እስትንፋሴ ሆነሻል አንዴ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *