ዳዊት ፅጌ – የኔ ዜማ / Dawit Tsige – Yene Zema

Dawit Tsiga

ፍቅር ነው መንገዴ
ይቅርታ ነው ልምዴ

ስኖር ከሱ በላይ
ምንም ነገር አላይ
የአበቦቹም ውበት ያልፋል
ብርቱም ያሉት ይሸነፋል
የሰማዩም የምድሪቱም
ፍቅር ላይ ነው መሰረቱ

ፍቅር ፍቅር ፍቅር

ዳገት ቁልቁለቱን ተራራውን በእግሬ … የኔ ዜማ ፍቅር
አሰለቸኝ ብጮህ ስለፍቅር ዞሬ … የኔ ዜማ ፍቅር
እሾህ አያስቆመኝ አይገታኝ ጋሬጣ … የኔ ዜማ ፍቅር
ሁሉን አልፈዋለሁ በፍቅር የመጣ … የኔ ዜማ ፍቅር

የኔ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር

እርካታ ነው ፍቅር ፀጋው
ተከባብሮ ለሚያወጋው
ውጤት አለው ሁሉም ነገር
ሰላም ፍቅር ሲሆን ሀገር

(የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር)2X

ፍቅር ነው መንገዴ
ይቅርታ ነው ልምዴ

ስኖር ከሱ በላይ
ምንም ነገር አላይ

በባለ እዳ አልነሳ
በፍቅር የተነሳ
ልገስግስ ይሙላው ቀኔን
ፅድቄ ፍቅር ምናኔ

ፍቅር ፍቅር ፍቅር

እንደ አክሱም ድንቅ ነው እንደ ላሊበላ … የኔ ዜማ ፍቅር
ከፊት የሚቀድም ያነፁት ከኃላ … የኔ ዜማ ፍቅር
ኖረውት አልፈዋል እነ ማቱሳላ … የኔ ዜማ ፍቅር
እድሜያቸው ይመስክር ያገኙትን ሰላም … የኔ ዜማ ፍቅር

የኔ ዜማ ፍቅር
የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር

እራሴን ላድን ከጥላቻው
በማለዳ በመባቻው
ጣይ ሳይመጣ ነቃሁና
ወደ ፍቅር ሄድኩኝ ደና

የኔ ዜማ ፍቅር
የልቤ ዜማ ፍቅር

Please follow and like us:
Tweet 20

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *