ዲጄ ሮፍናን – ልንገርሽ \ DJ Rophnan – Lingersh

DJ Rophnan

አንቺ ሰው ልገልፅሽ
ቃላት አጣሁልሽ
ጠፋና የምለው
ገና ሳልጀምረው

ልንገርሽማ
እንድታውቂው ልሞክር
ቃል ልደረድር
ከየት ብዬ ልጀምር
እ ልጀምር ነይ ነይ

ልንገርሽማ
ልገጥምልሽ ሞከርኩና
ቤቱን ከየት ልምታው
ያንቺ ፍቅር ቤት አይበቃው
እ አይበቃው ነይ ነይ

ልንገርሽማ
እችል መስሎኝ እዘርፈው
ቃላት ገጣጥሜ
እኔን ብሎ ባለቅኔ
ድንቄም ባለቅኔ ነይ ነይ

ልንገርሽማ
አቅቶኛል ልገልፅሽ
እንኳን ልክስሽ
ብቻ ይወድሻል ልጅሽ
አይ ልጅሽ ነይ ነይ

አይ ልጅሽ ይወድሻል ልጅሽ እምዬ
ሞትን ባስቀረው ላንቺ ብዬ
እማማዬ እማማዬ
ቃላቶች ስላጣሁልሽ ሙዚቃዬን
ፍቅሬን ልንገርሽ
እማማዬ እማማዬ

እ ማ ዬ

በላይ በላይ ላንቺ ደስታን ድርብርብ ያርገው
የሰማዩ ልቡ የታመነው
አሜን

ልንገርሽማ
ዛሬ ትልቅ ሰው ተብዬ ለሰው ልታይ እንጂ
ላንቺ የማላድግ ልጂ
ሁሌም ህፃን ልጂ ነይ ነይ

ልንገርሽማ
ያጠባሽው ግስላማ ማን ሰው ይችለዋል
ባንቺ ሲሉት ብቻ ይተዋል
ስምሽ ያበርደዋል ነይ ነይ

ልንገርሽማ
ድጋሚ ልፍጥርህ ብሎ ምርጫ ቢያቀርብልኝ
እንቺን እለው ድገምልኝ
አይ ድገምልኝ ነይ ነይ

ልንገርሽማ
አድጌያለው በእጆሽ
ሰው ነኝ በምክርሽ
ጠብቆኛል ፀሎትሽ
ፍቅሬ አንቺ ነሽ

እወቂው ይወድሻል ልጅሽ እምዬ
ሞትን ባስቀረው ላንቺ ብዬ
እማማዬ እማማዬ
ቃላቶች ስላጣሁልሽ
ሙዚቃዬን ፍቅሬን ልንገርሽ
እማማዬ እማማዬ

አ ደ ዬ

በ ላ ዬ

♥እ ና ና ዬ ♥

Please follow and like us:
Tweet 20

1 thought on “ዲጄ ሮፍናን – ልንገርሽ \ DJ Rophnan – Lingersh

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *