መለያየት ሞት ነው በሚለው ዘፍን …. በሚለው ዘፍን
በእምባ ታጥበን ነበር ስቴድ ተቃቅፈን … ስቴድ ተቃቅፈን
መሄድህን እንጂ መቅረትክን አላምነው .. መቅረትክን አላምነው
ዛሬ ነገ ሳትል ፍቅሬ ሳልሞትብህ ብትመጣልኝ ምነው

አሄ ሰው ሲያየኝ የተሸኮረመምኩተ
አሄ በዘፈን ማልቀስ የጀመርኩት
አሄ የፍቅር ደብዳቤ የፃፍኩት
ባንተ ነው ሁሉንም የሆንኩት

ካንተ ጋር በምሽት ደምቀናል
ካንተ ጋር በዝናብ ታጥበናል
ካንተ ጋር ተጣልተን ታርቀናል
ካንተ ጋር ሁሉንም ሆነናል

(በላኽው አንጀቴን በላኽው
እመጣለው ብለህ ሄደህ የቀረኸው) 2x

መለያየት ሞት ነው በሚለው ዘፍን …. በሚለው ዘፍን
በእምባ ታጥበን ነበር ስቴድ ተቃቅፈን … ስቴድ ተቃቅፈን
መሄድህን እንጂ መቅረትክን አላምነው .. መቅረትክን አላምነው
ዛሬ ነገ ሳትል ፍቅሬ ሳልሞትብህ ብትመጣልኝ ምነው

አሄ ፀሀይን ሲነጋ እምሞቃት
አሄ ጨረቃን ላይኔ የምናፍቃት
አሄሄ አበቦች ያልኩት ማማራቸው
ያኔነው ካንተጋር ሳያቸው

ካንተ ጋር አለም ትሞቃለች
ካንተ ጋር ቀኔ ትዋባለች
ካንተ ጋር ሁሉም ደስ ያሰኛል
ካንተ ጋር ሺ ዘመን ያንሰኛል

በላኽው አንጀቴን በላኽው
እመጣለው ብለህ ሄደህ የቀረኸው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *