ለማን አቤት ብዬ የት ሄጄ ልናገር
ዘመድ አዝማድ አላቅ ሰው የሌለኝ በሀገር
አንቺ ነሽ ጨረቃ ልቤን የምታውቂ
ይልቅ ከጎኔ ሁኚ ተይ አትደበቂ

ኧረ አይጣል ነው አይጣል ከመሸ ጨዋታ
አርቆ ከምትወስደኝ ካሰምጥከኝ ቦታ
ሁሌ ከመሻሸ ከንፈርህን ለምጄ
ሰዓቴን ጠብቄ ቆሚያለሁ ከደጄ

ፍቅር አስለምደኸኝ ሁሌ ከመሻሸ
ድንገት ዛሬ ብትቆይ ልቤን ተረበሸ

አፋልጊኝ ጨረቃ እስካገኘው ውዴ
ብርሀን ሁኚኝ ና ምሪኝ በመንገዴ /2x

ለማን አቤት ብዬ የት ሄጄ ልናገር
ዘመድ አዝማድ አላቅ ሰው የሌለኝ በሀገር
አንቺ ነሽ ጨረቃ ልቤን የምታውቂ
ይልቅ ከጎኔ ሁኚ ተይ አትደበቂ

ኧረ ናልኝ ናልኝ ፍጠንና
ተጨንቂያለሁ አውጣኝ ከፈተና
ቆሜ ማደሬ ነው ስጠብቅህ ደጃፍ
አማትራለሁኝ እዚም እዛም ሳላይ

ፃፍክልኝ ምሽቱን የኔ ድንቡል ዶቃ
አብሬው አድሬ በማን ይደነቃል
ብቻ አንተ ሁን ደና አይከብደኝ መጠበቅ
አይንህን አይቼ ከእቅፍህ እስክጠልቅ

አፋልጊኝ ጨረቃ እስካገኘው ውዴ
ብርሀን ሁኚኝና ምሪኝ በመንገዴ /2x

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *