አልቻልኩትም ዛሬ ደሞ ከትላንትናው
ለካ ስትመጪነው እኔ ደና ምሆነው
ሰላም ሆኜ ተጫውቼ አረፍ ልል ስል
በቃ ልሂድ ትይኛለሽ አይንሽን ሳልጠግብ

ደሞ ስናፍቅ ምን እሆን ይሆን
ካላገኘሁሽ ደስተኛም አልሆን
ቶሎ ድረሺ እንዳልከፋ
እናፍቃለው ነይ የኔ ተስፋ

ፍቅሬ ነይነይ ቶሎ
ቆንጆ ነይነይ ቶሎ
ልቤ አስቸገረኝ አንቺን አምጣ ብሎ

ቢቻልማ ነው ካንቺ ጋ
ቀን ሌት አልፎ እስኪነጋ
የሚወድሽ ሁሉም ሰው ነው
እንዴት ልሁን እፈራለሁ

(ያየሽ ሁሉ ወዶ ይመጣል መልሶ
መልሶ መላልሶ ያይሻል ደጋግሞ) 2x

ብሶብኛል ዛሬ ደሞ ከትላንትናው
ለካ ነበር ከልቤ ውስጥ የተደበቀው
እነጫነጭ ጀመር ውዴ አይንሽን ሳጣው
ይሄንን ፀባይ ታዲያ እኔ እንዴት ልልመደው

ደሞ ስናፍቅ ምን እሆን ይሆን
ካላገኘውሽ ደስተኛም አልሆን
ቶሎ ድረሺ እንዳልከፋ
እናፍቃለው ነይ የኔ ተስፋ

ፍቅሬ ነይነይ ቶሎ
ቆንጆ ነይነይ ቶሎ
ልቤ አስቸገረኝ አንቺን አምጣ ብሎ

የጨለማ ውብ ኮኮቤ
ፍቅርሽ ሁሌ ነው ከልቤ
የወደድሽኝ ያለምክንያት
ላንቺ ኖሬ ላቺስ ብሞት

(ያየሽ ሁሉ ወዶ ይመጣል መልሶ
መልሶ መላልሶ ያይሻል ደጋግሞ) 2x

ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ

ታምኜ ኖራለው ስታዘዝሽ ሁሌ
ካንቺ ሌላ ላላይ ምያለው በምዬ ምያለው በማዬ

(ያየሽ ሁሉ ወዶ ይመጣል መልሶ
መልሶ መላልሶ ያይሻል ደጋግሞ) 2x

2 Replies to “ሄኖክ ጌታቸው ከ ጊልዶ ካሳ – ብሶብኛል / Henok Getachew – Besobeshal”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *