ቅዱስ ላሊበላ ነው አሉኝ ቤቱ
ልሂድ ዓይን ዓይኑን ልየው ማልጄ
ላስታ ላሊበላ ነው አሉኝ ቤቱ
ልንገረው በዛው ልሳለም ሄጄ

ልሳለም … ልሳለም ውዴን
ፀሀይ ሳትወጣ ልያዝ መንገዴን
ልሳለም … ልሳለም ውዴን
ውዬ ደጁ ላይ ላውጋው የሆዴን

ማሬዋ ስክን ገላዋ ስክን ገላዋ ሆሆሆ
ማሬዋ ደርባባዬዋ ደርባባዬዋ ሆሆሆ

ህመም አባ ውዴ እኔ ያንተ ዝክር ገላ ሆይ
መንገድም እንዳልደክም ፍቅርህ ስንቅ አይሆንም ወይ
ትዝታህ እያጀበኝ ወዳንተ መገስገሴ
አንድም ለስጋዬ ነው አንድምለደሞ መንፈሴሴ
ሆሆሆ

በረታው በረታው ወዳንተ መጣው

ልሳል ልሳለም ቅዱስ ንጉሱን
ያውቀዋል ባንተ አንጀት ማራሱን
እያለኝ ልቤ አንድ አንተን ፍቱን
እንደምን ልፍራው ገደል ዳገቱን

ማሬዋ ስክን ገላዋ ስክን ገላዋ ሆሆሆ
ማሬዋ ደርባባዬዋ ደርባባዬዋ ሆሆሆ

ቅዱስ ላሊበላ ነው አሉኝ ቤቱ
ልሂድ ዓይን ዓይኑን ልየው ማልጄ
ላስታ ላሊበላ ነው አሉኝ ቤቱ
ልንገረው በዛው ልሳለም ሄጄ

ልሳለም … ልሳለም ውዴን
ፀሀይ ሳትወጣ ልያዝ መንገዴን
ልሳለም … ልሳለም ውዴን
ውዬ ደጁ ላይ ላውጋው የሆዴን

ማሬዋ ስክን ገላዋ ስክን ገላዋ ሆሆሆ
ማሬዋ ደርባባዬዋ ደርባባዬዋ ሆሆሆ

ደጀ ሰላሙ ላይ ትቼው ለአምላኬ ነፍሴን
ውዬ አብሬ በመስኩ ሳድብ ሳድስ መንፈሴን
ፋኖስ ላንባዬን ይዤ ከሶሮው ላይ ማምሸቴ
አስማምቶኝ ነው ከፍቅርህ ምክራቸው ቄስ እሸቴ
ሆሆሆ

በረታው በረታው ወዳንተ መጣው

ልሳል ልሳለም ቃኝቼው ልግባ
ሰርኬ አንተ ንፁህ ውቅር ድንቅ አንባ
ሳርም ሳበጃጅ ውዬ ደጅህ
አለብኝ ጉዳይ እማዋይህ

ማሬዋ ስክን ገላዋ ስክን ገላዋ ሆሆሆ
ማሬዋ ደርባባዬዋ ደርባባዬዋ ሆሆሆ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *