አቤት አቤት አቤት
አቤት የሷስ ውበት
ከተማው ያራዶች ቤት
ሁሉንም በሷ ውበት

ጩኸት ያስተጋባል የገደል ማሚቱ
እሷን ብዬ ጮውኩኝ የታለች ልጅቱ

ንጠው ንጠው ለዩት አይቡን ከአሬራ
መብከንከኔን አውቆ ጠፋ የሚያወራ

ድኙን አጨሱልኝ በሽታ መስሏቸው
እሷ እንዳመመችኝ ማን በነገራቸው

እንዴት ያረጉታል የሆድን ህመም
ማጭድ አይገባበት በእጅ አይታረም

ጫካውን አልፈራ ከዱሩ ዘልቄ
አውሬ ቢያጓራብኝ ድንቄ አይደለ ብርቄ
ሰዉን ጉድ አስባለው አንቺን ስል መውደቄ
ቅረቢኝ ከጎኔ እንደ ግርማ ሞገስ
እንጀራም ያለ አይን መች ይልና ደስ

ያንቺስ ውዴ ክፉኛ ከባድ ነው
አንቺን ብቻ ሌት ተቀን የምለው
አቤት አቤት ባንቺ ስንቱን አየው
አቤት አቤት ብዙ ተሰቃየው

(አቤት አቤት) 4x

አቤት አቤት….. መውደድ አቤት አቤት
አቤት አቤት …. ፍቅር አቤት አቤት

የስሜቴ ጌታ የልቤ ባለቤት
የምወዳትን ልጅ አርግልኝ ጎረቤት

አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት

ሰበዝብ ሰንበሌጥ ፊደል ነው የለያቸው
መውደድም ፎንቃ ነው ሲቀፀል ያው ናቸው

ጠዋት ያዩት ጤዛ ማታ ቢሰለብም
ልብ የገባን ፍቅር ማውጣት አይታሰብም

ኬሻውን አንጥፌ ከደጇ ልተኛ
ቅዠቱ ባይተወኝ ጋብ ይበልልኛ

ካቻማሌው መጣ ተጉዞ ተጉዞ
አይኗ ሆነኝ ጠላት አፍዞ አደንግዞ
ጥርሷም አሰከረኝ ወዝውዞ ወዝውዞ

የታለ ሹማምንት የታሉ ጌቶቹ
ከአንጀት አማካሪ ጠፉ ጠቢቦቹ

ዝናር ከወገቡ የማይጠፋው ጀግና
ትጥቁን አስፈታሽው ሆነሽው ፈተና

ያንቺስ ውዴ ክፉኛ ከባድ ነው
አንቺን ብቻ ሌት ተቀን የምለው

አቤት አቤት ባንቺ ስንቱን አየው
አቤት አቤት ብዙ ተሰቃየው

( አቤት አቤት ) 4x

አቤት አቤት….. መውደድ አቤት አቤት
አቤት አቤት …. ፍቅር አቤት አቤት
የስሜቴ ጌታ የልቤ ባለቤት
የምወዳትን ልጅ አርግልኝ ጎረቤት

አይን አይከሰስ ደሞ በማየት
እዳው ለልብ ነው እንደ ሞት ሽረት
ከውቢቷ ዘሮች የሴት እመቤት
ስሜም ባንቺ ይጥፋ ስጠራሽ አቤት

(ስጠራሽ አቤት) 4x

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *