ሳያት_ደምሴ – እስክሽር / Sayat Demssie – Eskesher

Single

እየታወሰኝ ነው ቃልኪዳን ስትገባ
አይኖችህ በእውነት ተሞልተው በእንባ
አምኜው ሲናገር ልቤን ብረታለት
እሱ ተጫወተ በቃል በቀለበት

ፍቅርህ አሸንፎኝ ተሞኘሁኝ ወይኔ
ጨዋታ ነው ላንተ እንደዛ መሆኔ
መሬት አይንካሽ ሲል እንዳልነበር ያኔ
የ እግ’ዜሩ ሰላምታ አጥሮህ አየሁ ለኔ

ለመርሳት የሚሆን አቅም ባይኖረውም ገላዬ
ገላዬ ..ገላዬ

ላልቅስልህ ላውርድ ይፍሰስልህ እንባዬ
እንባዬ እንባዬ

በምችለው ልካስ ላልቅስልህ ባይኔ
ላልቅስ ላልቅሰው ባለው በአቅሜ
ሳቄን ለሰው ሰጠህ ቀምተኸኝ ከኔ
አሁን አቅም የለኝ ላንተ የሚበቃ

ፍቅርህ እንዲቀለኝ ጉልበቴ ነው እንባ ..ጉልበቴ ነው እንባ

ይብላኝ እንጂ ላንተ ለሄድከው በባዶ
እኔስ ፍቅር አለኝ አልሆንኩም ጎዶሎ
አሁንም ይወራል ትተኸኝ መሄድህ
ማን በነገራቸው መንገድ ነው ቅጣትህ

አየሁትን ፍቅርህን ከቀለበት ሾልከህ
እንዲያው ያወጣሀው ቃላት አልከበደህ
ኧረረረ.

እንዴት ቀሎብህ ነው እንዴት ቢታይህ
የኔ መሆን ያነሰብህ ኧረ ረረ
ልብህ ግንድ ብቻ አያፈራ ፍሬ
በምችለው ባለኝ ላልቅስለህ ባይኔ
ላውርደው እምባዬን ላልቅስ ላንጎራጉር
በአባ መላ ጊዜ ከህመሜ እስክሽር
ግን ትንሳኤው ቅርብ ነው ለተረታ በፍቅር
እህእህእህ

ለመርሳት የሚሆን አቅም ባይኖረው ገላዬ
ላልቅስልህ ላውርድ ይፍሰስልህ እምባዬ
ላልቅስልህ ላውርድ ይፍሰስልህ እምባዬ

Please follow and like us:
Tweet 20

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *