አያምጣዉ ነዉ እንጂ አያድርስ
የሰዉ ሰዉ ተወዶ የታል ክስ
ምነዉ ፍቅርህ ትጥቄን ሊያስፈታ
በኔዉ በጭምቷ በረታ

ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ምነዉ በሆንኩኝ ግድ የለሽ
ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ልቤን ከፍቅርህ እንዳሸሽ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

በማላዉቀዉ ነገር ድንገት
ተሰብስቤ ካለሁበት
ባትነካካኝ ምን አለበት
ምነዋ ምነዋ

በማለዳዉ ፍቅር ገብቶ
ልቤን በአንተ አስደስቶ
የነገርከኝን ሰንብቶ
ምነዋ ምነዋ

ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ምነዉ በሆንኩኝ ግድ የለሽ
ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ልቤን ከፍቅርህ እንዳሸሽ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

አያምጣዉ ነዉ እንጂ አያድርስ
የሰዉ ሰዉ ተወዶ የታል ክስ
ምነዉ ፍቅርህ ትጥቄን ሊያስፈታ
በኔዉ በጭምቷ በረታ

ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ምነዉ በሆንኩኝ ግድ የለሽ
ባንተ ቦታ ቢያደርገኝ
ልቤን ከፍቅርህ እንዳሸሽ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

ፅኑ ፍቅሬም ላያባራ
ምኞት ህልሜን ላትጋራ
ልቤን ባልሰጥ ላንተ አደራ
ምነዋ ምነዋ

ይቀል ይሆን በምን ብርታት
ሁለት ፀፀት ሁለት ቅጣት
አንተን ማግኘት አንተን ማጣት
ምነዋ ምነዋ

አድሮ እንደጥርስ ህመም ለሚጠዘጥዘኝ
ለዚህ ለዚህ ነዉ ወይ ያንተ ፍቅር የያዘኝ
በቅናት ላይ ቅናት እየደጋገመኝ
ስንቴ ሞቼ ነበር ሳልል አመመኝ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

አይኔ በል ተዉ አትይ የሰዉ
ልቤ በል ተዉ አትበል የሰዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *