ደሞ በአባይ ድርድር
ደሞ በአባይ …
ማን ዝም ይላል ሆኖ ዜጋ
ደሞ በአባይ …
አባይ አባይ …

ቼ በለው ኧረ ቼ በለው 2x

ቼ በለው >>አባቱም ገዳይ
ቼ በለው >> እናቱም ገዳይ
ቼ በለው >> ድርድር አያውቅም
ቼ በለው >> በሃገሩ ጉዳይ
ቼ በለው >> አባይ የግሌን
ቼ በለው >> ባልኩኝ ለጋራ
ቼ በለው >> ካቃራት ምስር
ቼ በለው >> ግፍም ሳትፈራ
ቼ በለው >> የተቆጣ እንደው
ቼ በለው >> ፍቅር ታግሶ
ቼ በለው >> የሚባላ እሳት
ቼ በለው >> ይሆናል ብሶ

ቼ በለው ኧረ ቼ በለው 2x

ማን ዝም ይላል ሆኖ ዜጋ
ደሞ በአባይ …
አባይ … አባይ …

ሳንጃው ፀብ አይመርጥም 2x

ልቁረጠው አለ እንጅ
የራሴን ውሃ ጥም

ሳንጃው ፀብ አይመርጥም 2x

ይሁን ይበጅ
ለኔም ለርሷም ብዬ እንጅ
ሯ .. ሯ .. ሯ ..
ማንንም አልፈራ

ቼ በለው ኧረ ቼ በለው 2x

ቼ በለው >> አባይ ለጋሱ
ቼ በለው >> ግብፅን አርሶ
ቼ በለው >> አገሬን ባለቼ
ቼ በለው >> ልይ ተመልሶ
ቼ በለው >> ብሎ አሻፈረኝ
ቼ በለው >> ለሳበ ቃታ
ቼ በለው >> እኔን አያርገኝ
ቼ በለው >> የነካኝ ለታ

ቼ በለው ኧረ ቼ በለው 2x

ተው … ተው … ተው …

ደሞ በአባይ ድርድር
ደሞ በአባይ …

[ከእንግዲህ አይኖርም ነገር ማለሳለስ
ማን ዝም ይላል ሆኖ ዜጋ]2x

ደሞ በአባይ ድርድር

ከሞከሩንማ ደፍረው እዚህ ድረስ
ዋ…ዋ…ዋ
ማን ዝም ይላል ሆኖ ዜጋ

ተው … ተው … ተው …

ተው ሲሉት ካልሰማ አሳደክ በለው
በአባትህ ጎራዴ በተሰቀለው

ማን ዝም ይላል ሆኖ ዜጋ
አባይ አባይ …

እያመመው መጣ >> እያመመው
እያመመው መጣ >> አለፈ ገደፉን
እያመመው መጣ >> ትዕግስቴ ልክ አጣ
እያመመው መጣ >> እንኳን ለጎረቤት
እያመመው መጣ >> ከወንዜ ለጠጣ
እያመመው መጣ >> ቋያ እሳት ነው ክንዴ
እያመመው መጣ >> ከሩቅም ለመጣ
እያመመው መጣ >> አስተምረዋለሁ
እያመመው መጣ >> ታሪኬን ከጥንቱ
እያመመው መጣ >> እስኪፈራኝ ድረስ
እያመመው መጣ >> የሞተው አባቱ

ተው … ተው … ተው …
ደሞ በአባይ ድርድር
ደሞ በአባይ …
ተው ሲሉት ካልሰማ አሳደክ በለው
በአባትህ ጎራዴ በተሰቀለው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *