ሁኔታ ይፈትናል ፈተና ሰውን ይለያል
ጊዜ ፈራጅ ሁሉን ያያል
ጎበዝን ከውድቀት ያስጥላል
ይቆጠራል ደቂቃ ይመዘናል
ሁሉን ለህልሙ የሰጠ መድረስን ይታደላል

ሁሌ … ሁሌ

አሻግሬ እያየሁ
እያየሁ … እያየሁ
መምጫሽ ያጓጓኛል
ሁሌ

እናፍቅሻለሁ
ናፍቃለሁ… ናፍቃለሁ
ህልሜ መንጎድሽ ቀጥ ማቋረጫም የለው
ይታየኛል ጫፉ ጉዞዬም ግድ ነው
ተስፋ መቁረጥ አላውቅ የለም ከመዝገቤ
ውላለው አድራለው ከትላንት ቀርቤ

ሁሌ ሁሌ

አሻግሬ እያየሁ

እያየሁ እያየሁ
መምጫሽ ያጓጓኛል
ሁሌ
እናፍቅሻለሁ
ናፍቃለሁ ናፍቃለሁ

መቼ ነው ቁጭ ብለን ሳለፈው ምንስቀው
ሳናስብ በሆነው አልመን ባጣነው
መንገርን እሻለው ያለፍኩትን ሁሉ
መጥረግ ለሚመጣው ምኞቴ ሆኖ ሙሉ

ዋናው አሻግሮ ማየት መቻል ብቻ ነው ነው ነው ነው
መሮጥ መድከም መውደቅ መሰበርም አለው

ዋናው አሻግሮ ማየት መቻል ብቻ ነው ነው ነው ነው ነው
መሮጥ መድከም መውደቅ መሰበርም አለው

Sሀe he since the first day
I saw a dream him
Me deya dey sittin up on my sit
And so, oh, ain’t no way I’m losing hope
I know all of me stairs I’m goin up

ከራስ ውድድር ነው ዓለም
መነሻም ባይታይ መድረሻን ሚገድብ የለም

ሌላ ሚያሻትም የለም
ቁርስህን ተስፋ ምሳህን ጥረት
እራት ትሰጥሃለች ደግሞ ዓለም

Fire fire pushing me into your direction
Higher Higher
Me know that’s my destination
Am not liar liar
There gonna be some sufferation
But hope in my mind no distraction

ሁኔታ ይፈትናል ፈተና ሰውን ይለያል
ጊዜ ፈራጅ ሁሉን ያያል
ጎበዝን ከውድቀት ያስጥላል
ይቆጠራል ደቂቃ ይመዘናል
ሁሉን ለህልሙ የሰጠ መድረስን ይታደላል

ቀናው አሻግሮ ማየት መቻል ብቻ ነው

[ዋናው አሻግሮ ማየት መቻል ብቻ ነው
መሮጥ መድከም መውደቅ መሰበርም አለው] 5x

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *