ብጠራኝማ አለው አቤት
ስትልከኝ ማለቴም ወዴት
የኔ መውደድ ላንተ በደል
አርጎት ነበር ለካ ቀለል

ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ዋ ለኔ ዋ ለኔው

ያሻግርህ ያሻግርህ
ያሻግርህ ምን አለ
ያንተ መልካም ለኔ በትዝታ እስካለ
ካሻ ኑር ካሻ ኑር ይሙላልህ ያሰብከው
ደጉን ገላ ለምደህ የኔን ክፉ ካልከው

ከንፈር መምጠጥ መፀፀቱ
ባያስጥልም ከትዝብቱ
የኖሩት ቃል በሰቀቀን
ግርም ይላል ትዝ ያለ ቀን

ገረመኝ ገረመኝ
ገረመም ግር አለኝ
ትዝታን በስለት መቁረጥ ቢቸግረኝ

አመመኝ አመመኝ
አመመኝ በፅኑ
የኔ ልብ እንዳንተ አለመደንደኑ

ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ዋ ለኔ ዋ ለኔው

ብጠራኝማ እላለው አቤት
ስትልከኝ ማለቴም ወዴት
የኔ መውደድ ላንተ በደል
አርጎት ነበር ለካ ቀለል

ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ዋ ለኔው ዋ ለኔው

ያሻግርህ ያሻግርህ
ያሻግርህ በግዜ
መውደድ እስካረገኝ የትዝታ ሚዜ
ካሻ ኑር ካሻ ኑር ባሰብክበት ቦታ
ደፋ ቀና እላለው እኔው ለኔ ደስታ

ከንፈር መምጠጥ መፀፀቱ
ባያስጥልም ከትዝብቱ
የኖሩት ቃል በሰቀቀን
ግርም ይላል ትዝ ያለ ቀን

ገረመኝ ገረመኝ
ገረመም ግር አለኝ
እርሙሙ ስቶ ሆዴ
አንተን አንተን ሲለኝ
ሙሾ ባላሶርድ ደረቴን ባልመታ
አልቅሼው የለም ወይ ሳጣህ መንታ መንታ

ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ያማል ቅኔው
ዋ ለኔው ዋ ለኔው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *